የረቡዕ ትምህርት ፕሮግራም

     እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” ማቴ ፡28፥19-20

በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን የተሰጠውን ታላቁን ተልእኮ ከመፈጸም አንጻር የናዝሬት ቁጥር 2 ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ በወንጌል እውነት አምነው የዳኑትን አማኞች ጌታን የሚመስሉ እውነተኛ ደቀመዝሙር ለማድረግ ከምትጠቀምበት አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ በትምህርት እና ስልጠና አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ ከሚገኙት በአንዱ ሳምንታዊ የአገልጋዮችና ምእመናን ትምህርት ፕሮግራም ነው፡፡

ፕሮግራሙ የሚከናወነው በየሳምንቱ እሮብ ማምሻውን 1130-100 ሲሆን ትምህርቱ በተለያዩ ርእሶች ላይ በቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና በተጋባዥ አገልጋዮች ይሰጣል

በፕሮግራሙ ውስጥ ፦

  • በተሰጠው ትምህርት ላይ የጥያቄና መልስ
  • የውይይት
  • የጸሎት ፕሮግራም ይደረጋል፡፡

በዚህም መሰረት ፕሮግራሙ ለቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን በእግዚአብሄር ቃል መታጠቅና ከፍተኛ መነቃቃት አምጥቷል፡፡

ክብር ሁሉ ለእግዚአብሄር ይሁን!

“እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤”  ቆላስይስ ፡ 1፥28